የፓን አፍሪካ ወጣት አመራሮች ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄድ ጀመረ
12:10 03.04.2025 (የተሻሻለ: 12:34 03.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፓን አፍሪካ ወጣት አመራሮች ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄድ ጀመረ
ጉባኤው "የወጣቶችን አቅም - ለበለፀገች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ ከመጋቢት 25 እስከ 27 ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይካሄዳል፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የሴቶችና እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሀት ካሚል፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት አመራሮች፣ የወጣት ሚኒስትሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ሌሎችም የጉባኤው ተሳታፊ ናቸው።
በጉባኤው የጅቡቲ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኬኒያ፣ የአልጄሪያ፣ የብሩንዲ እና የቦትሶዋና ተወካዮች እንደሚሳተፉ በስፍራው ላይ የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
