ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያስገድድ አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ
10:50 03.04.2025 (የተሻሻለ: 11:24 03.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያስገድድ አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያስገድድ አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ
"የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ታቅዷል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ አሠራሩ በሀገሪቱ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንደሚቀርፍ አስረድተዋል። በሀገሪቱ 100 ሺህ የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩን በተደረገ ግምገማ መታወቁን ተናግረዋል፡፡
በአሠራሩ መሠረት በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ከሰጠ በኋላ እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡
ሙያው ላይ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል መምህራን በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ "የመምህራን ባንክ" ለማቋቋም ታቅዷል፡፡
@sputnik_ethiopia