የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.04.2025
ሰብስክራይብ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ

አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበትን 14ኛ ዓመት አስመልክቶ በኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ባሳተሙት ፅሑፍ ግድቡ የሀገሪቱን ኩራት እና ቁርጠኝነት የተላበሰ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

የህዳሴ ግድብ ዘላቂ ኃይል፣ ውሃ፣ ምግብ እና የሥነ ምህዳር የመቋቋም አቅምን የማረጋገጥ አቅም እንዳለውም ተናግረዋል። ግድቡ ቀጣናዊ ገፅታም አለው ያሉት አምባሳደሩ፤ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር ንፁህ ኃይል ማቅረብ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

የሩሲያው አምባሳደር አክለውም የታለቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት እንደሚያፋጥን እንዲሁም ለድንበር ዘለል የውሃ አስተዳደር እና ለአፍሪካ የመሠረተ ልማት ግንባታ ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ገልፀዋል።

"ግድቡ አሁን ያለው ትውልድ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደሚችል የሚያስመሰክር ነው" ብለዋል አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ንግግር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ማለታቸው የሚታወስ ነው።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0