የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና የኤም23 አማፂያን በሚቀጥለው ረቡዕ የመጀመሪያ የቀጥታ ውይይት ሊያደርጉ ነው
18:27 02.04.2025 (የተሻሻለ: 18:54 02.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና የኤም23 አማፂያን በሚቀጥለው ረቡዕ የመጀመሪያ የቀጥታ ውይይት ሊያደርጉ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና የኤም23 አማፂያን በሚቀጥለው ረቡዕ የመጀመሪያ የቀጥታ ውይይት ሊያደርጉ ነው
"ሌላኛው ወገን እስካልጣሰው ድረስ" ድርድሩ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ይካሄዳል ሲሉ አንድ የኮንጎ ባለሥልጣን ለብሪታንያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ የኤም23 ምንጭ ጥያቄዎቻቸውን ለኪንሻሳ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ወገኖች ውይይቱን በሚስጢር ለመጠበቅ እንደተስማሙ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የታቀደው ውይይት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ እና የሩዋንዳ አቻቸው ፖል ካጋሜ መጋቢት 11 ቀን በዶሃ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
የኳታር አሸማጋዮች የኮንጎ እና ሩዋንዳን ሁለተኛ ዙር ምክክር ባሳለፍነው አርብ ያስተናገዱ ሲሆን በተናጠል ከኤም23 ተወካዮች ጋርም እንዲሁ ተገናኝተዋል።
@sputnik_ethiopia