የናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች
የናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.04.2025
ሰብስክራይብ

የናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሪ ትሩትኔቭ ከናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር "የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት በሩሲያ-ናሚቢያ የበይነ መንግሥታት የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ የትብብር ኮሚሽን ጥላ ሥር እያደገ ቀጥሏል። አስደናቂ ውጤቶችንም ማስመዝገብ ችለናል” ብለዋል።

ባለሥልጣኑ ሩሲያ በታህሳስ ወር በመንግሥታዊ ኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ የቀረቡ እቅዶች በናሚቢያ በኩል በፍጥነት ተግባራዊ ይደረጋሉ ብላ እንደምትጠብቅ ገልጸዋል።

⏭ በናሚቢያ ዊንድሆክ ለመካሄድ የታቀደው አስራ አንደኛው የኮሚሽኑ ስብሰባ ዝግጅት ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ነበር።

"የሩሲያ-ናሚቢያ የበይነ መንግሥታት የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ የትብብር ኮሚሽንን ለማስተናገድ በናሚቢያ በኩል የቀረበውን ሀሳብ እንጠብቃለን። ከናሚቢያ ጋር ያለንን ግንኙነትም የበለጠ እናጠናክራለን። ሀገሮቻችን የቆየ ወዳጃዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ሩሲያ የናሚቢያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች" ሲሉ ትሩትኔቭ አፅናኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የናሚቢያ እና ሩሲያ የንግድ ግንኙነት በ2024 ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ሞስኮ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0