ኮሎምቢያ ለኪዬቭ የተሰለፉ ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ተገድለዋል አለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኮሎምቢያ ለኪዬቭ የተሰለፉ ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ተገድለዋል አለች
ኮሎምቢያ ለኪዬቭ የተሰለፉ ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ተገድለዋል አለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.04.2025
ሰብስክራይብ

 ኮሎምቢያ ለኪዬቭ የተሰለፉ ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ተገድለዋል አለች

"በዩክሬን የጦር ኃይሎች ውስጥ እየተዋጉ የሞቱ ኮሎምቢያውያንን የተመለከተ መረጃ ለማግኘት ዘመዶቻቸው ለኮሎምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ያቀርባሉ። ወደ 70-80 የሚሆኑ ኮሎምቢያውያን እንደሞቱ እናውቃለን" ሲሉ በሩሲያ የኮሎምቢያ አምባሳደር ሄክቶር አሬናስ ኔይራ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ አክለውም በግጭቱ ምን ያህል ኮሎምቢያውያን እየተሳተፉ እንደሚገኝ ግልጽ አይደለም ብለዋል።

"በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ ኮሎምቢያውያን በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ባለው ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ እንደሆነ አይተናል። ዩክሬን የተወሰነ መረጃ አላት፤ ሩሲያ ደግሞ የራሷ ቁጥር አላት። ኮሎምቢያ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መረጃ የላትም። ድርጊቱ በመንግሥት የማይደገፍ፤ በተቃራኒው የምናወግዘው ጉዳይ ነው" ሲሉ ዲፕሎማቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በርካታ የኮሎምቢያ ዜጎች በሩሲያ ባለሥልጣናት የተያዙባቸው አጋጣሚዎች እንደነበሩ አስታውቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0