የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ "በቂ ምግብ አለ" ማለቷን "አስቂኝ" ሲል ገለፀ
15:04 02.04.2025 (የተሻሻለ: 15:34 02.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ "በቂ ምግብ አለ" ማለቷን "አስቂኝ" ሲል ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ "በቂ ምግብ አለ" ማለቷን "አስቂኝ" ሲል ገለፀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ማክሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "የምግብ እና የቁሳቁስ አቅርቦቶቻችን እያለቁ ነው" ብለዋል።
የተመድ መግለጫ የእስራኤል የእርዳታ አቅርቦት ኤጀንሲ "ሃማስ ንፁሃን እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ከሆነ ለረጅም ጊዜ የሚሆን በቂ ምግብ አለ" ማለቱን ተከትሎ የመጣ ነው።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በመጋዘኖቹ ውስጥ ዱቄት ማለቁን እና እስራኤል መተላለፊያዎችን እንደገና እስክትከፍት እና አቅርቦቶች እስኪገቡ ድረስ ዳቦ ቤቶቹ መሥራታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ አስታውቋል። ዱጃሪክ ዳቦ ቤቶቹ የተዘጉት "ለቀልድ" አይደለም ብለዋል።
@sputnik_ethiopia