የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያን የንግድ ማዕከልነት አሳድጓል ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተናገሩ
14:44 02.04.2025 (የተሻሻለ: 15:04 02.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያን የንግድ ማዕከልነት አሳድጓል ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያን የንግድ ማዕከልነት አሳድጓል ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተናገሩ
ከመንግሥት ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ የነበራቸው በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ ከጅማሮው ጀምሮ የኢትዮጵያን እድገት እና ዘመናዊነት በማፋጠን ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተናግረዋል።
ለአብነትም ቻይና በአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመር፣ በመንገድ ዝርጋታ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሌሎች ቁልፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ መወዕለ ነዋይ እንዳፈሰሰች አንስተዋል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የግብርና እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እድገት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።
"በአጠቃላይ ይህ ተነሳሽነት የኢትዮጵያን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ቀጣናዊ ማዕከልነት በማጠናከር ለሀገሪቱ እድገት እና ዘመናዊነት አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ሲሉ" ተናግረዋል።
እ.አ.አ 2013 በፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ይፋ የተደረገው የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ፤ የመሠረተ ልማት ጉድለቶችን በመሙላት በእስያ ፓሲፊክ፣ አፍሪካ እንዲሁም በማዕከላዊ እና ምስራቅ አውሮፓ የኢኮኖሚ እድገት የማፋጠን ዓላማ አንግቧል።
@sputnik_ethiopia