በሄይቲ የሚገኙ የኬንያ ፖሊሶች ተከታታይ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ተባለ
11:37 02.04.2025 (የተሻሻለ: 11:54 02.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሄይቲ የሚገኙ የኬንያ ፖሊሶች ተከታታይ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ተባለ
በሄይቲ የተሠማሩ ሁለት ኬንያውያን ፖሊሶች ባለፈው ሳምንት ከወንበዴ ቡድኖች ጋር በተካሄደ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአብዛኛው ከኬንያ የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ወታደሮችን ያቀፈው የጋራ የጸጥታ ድጋፍ ተልዕኮ በ2026 ከሚደረገው ምርጫ በፊት የሄይቲን የጸጥታ ሁኔታ የመመለስ ዓላማ ተሰጥቶታል። ሆኖም የጥቃቶቹ ብዛት እና የበቂ መሳሪያዎች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የተልዕኮው ቃል አቀባይ ጃክ ኦምባካ በሰጡት አስተያየት "በየትኛውም ተልዕኮ አንዳንድ ጊዜ ጉዳት መድረሱ የማይቀር ነው" ያሉ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው መኮንኖች ለሕክምና እርዳታ ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ተልከዋል ብለዋል።
ሪፖርቱ አክሎም ፓሊሶቹ ሁለት ግዜ ጥይት በስቷቸዋል ያሏቸውን 20 ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ለመጠቀም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጿል።
የተልዕኮው አባላት በመከላከያ ትጥቆች ዙሪያ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ዋሽንግተን እንደሚጓዙ ሁለት ከፍተኛ የተልዕኮው መኮንኖች ለሚዲያ ተናግረዋል።
@sputnik_ethiopia