ሁቲዎች በሰሜን ምስራቅ የመን የአሜሪካን ኤምኪው-9 ሰው አልባ አውሮፕላን ሀገር ውስጥ በተሠራ ሚሳኤል መትተው መጣላቸውን ተናገሩ
17:47 01.04.2025 (የተሻሻለ: 18:04 01.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሁቲዎች በሰሜን ምስራቅ የመን የአሜሪካን ኤምኪው-9 ሰው አልባ አውሮፕላን ሀገር ውስጥ በተሠራ ሚሳኤል መትተው መጣላቸውን ተናገሩ
የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ የአሜሪካ የስለላ ሰው አልባ አውሮፕላን በማሪብ ግዛት የአየር ክልል ውስጥ እንደተመታ ተናግረዋል፡፡
የየመን የአየር መከላከያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አስራ ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በተሳካ ሁኔታ መትቶ መጣሉን ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡
ሁቲዎች በቀይ ባህር ላይ ዩኤስኤስ ሃሪ ትሩማን አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብን በ24 ሰዓት ውስጥ ሶስት ጊዜ ዒላማ አድርገው እንደነበር እሁድ እለት ተናግረዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባስተላለፉት ማስጠንቀቂያ የአሜሪካ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት የማያቆሙ ከሆነ 'ሁቲዎችም ሆነ ደጋፊዎቻቸው እውነተኛው ህመም ይጠብቃቸዋል' ብለዋል።
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ቪዲዮዎች ኤምኪው-9 የሰው አልባ አውሮፕላን ተመትቶ ሲወድቅ ያሳያል
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሁቲዎች በሰሜን ምስራቅ የመን የአሜሪካን ኤምኪው-9 ሰው አልባ አውሮፕላን ሀገር ውስጥ በተሠራ ሚሳኤል መትተው መጣላቸውን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/