የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ዘርፍ ባለፉት 6 ወራት 366 ሚሊዮን ዶላር እንዳስገኘ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
16:36 01.04.2025 (የተሻሻለ: 17:44 01.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ዘርፍ ባለፉት 6 ወራት 366 ሚሊዮን ዶላር እንዳስገኘ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ሚኒስቴሩ ይህን ያለው ዛሬ በተከፈተው ዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር ዐውደ-ርዕይ ነው፡፡ በዐውደ-ርዕዩ ላይ ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስትር ግርማ አምንቴ የሆርቲካልቸር ንዑስ ዘርፍ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ዘርፉ ስልጠና የሚፈልጉ እና ስልጠና የማያስፈልጋቸው የሥራ እድሎችን እንደፈጠረ ገልፀዋል፡፡ ከተፈጡሩት የሥራ እድሎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው በሴቶች እንደተሸፈነም አስታውቀዋል፡፡
ዐውደ-ርዕዩ “ሆርቲካልቸር ለዘላቂ ሀገራዊ ግብ” በሚል መሪ ሐሳብ በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ምስሎቹ በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተነሱ ናቸው
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ