ቻይና አሜሪካ የኒውክሌር ስጋቶችን እንድትቀንስ እና ሚሳኤሎችን ማሰማራቷን እንድታቆም አሳሰበች
13:21 01.04.2025 (የተሻሻለ: 13:44 01.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቻይና አሜሪካ የኒውክሌር ስጋቶችን እንድትቀንስ እና ሚሳኤሎችን ማሰማራቷን እንድታቆም አሳሰበች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻይና አሜሪካ የኒውክሌር ስጋቶችን እንድትቀንስ እና ሚሳኤሎችን ማሰማራቷን እንድታቆም አሳሰበች
የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ የአሜሪካን የኒውክሌር ፖሊሲዎች የተቹ ሲሆን ዋሽንግተን በአቶሚክ የጦር መሳሪያ ላይ ያላትን መተማመን እንድትቀንስ እና በዓለም አቀፍ ደህንነት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ድርጊቶች እንድትቆጠብ ጠይቀዋል።
ዋንግ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለ መጠይቅ የአሜሪካን "የኒውክሌር መጋራት"፣ በሌሎች ሀገራት ድንበር አቅራቢያ ሚሳኤል ማሠማራትን እና የሚሳኤል መከላከያ መስፋፋትን አውግዘዋል።
ዋንግ ዪ "ዋሽንግተን የኒውክሌር ጦርነት አደጋዎችን ለመቀነስ እና ፕላኔታችንን ከኒውክሌር ነፃ ለማድረግ በቂ ጥረት እንድታደርግ እንጠይቃለን" ብለዋል።
@sputnik_ethiopia