ፓርላማው የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገውን የማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ
11:12 01.04.2025 (የተሻሻለ: 11:34 01.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፓርላማው የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገውን የማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፓርላማው የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገውን የማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ
አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 በማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡
አዋጁ የፌደራል መንግሥት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ማሻሻያው የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደርን የስልጣን ዘመን ለማራዘም የተደረገ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
@sputnik_ethiopia