ኢትዮጵያ የኬኒያን የኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት እንደተቆጣጠረች ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የኬኒያን የኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት እንደተቆጣጠረች ተገለፀ
ኢትዮጵያ የኬኒያን የኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት እንደተቆጣጠረች ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የኬኒያን የኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት እንደተቆጣጠረች ተገለፀ

የኬኒያ የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ባለፈው ሳምንት እንደገለፀው ከውጭ ከሚገባው የኤሌትሪክ ኃይል ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች።

እስከ ታህሳስ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ኬኒያ ከውጭ ካስገባቸው ኤሌትሪክ ኃይል 84.9 በመቶው በኢትዮጵያ የተሸፈነ ሲሆን ኡጋንዳ 14.8 በመቶውን የታንዛኒያው ታኔስኮ ኩባንያ ደግሞ  0.24 በመቶውን ሸፍነዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ የምትልከው የኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛው የጨመረው እ.አ.አ በ2022 ኬኒያ ፓወር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከደረሱት ስምምነት በኋላ እንደሆነ የኪኒያ ሚዲያ በዘገባው አመላክቷል።

በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ የጀመረች ሲሆን ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ይህን መጠን ወደ 400 ሜጋ ዋት እንደሚያሳድጉት ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በኬኒያ በኩል ወደ ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ለማድረግ ሂደቶችን መጀመሯም የሚታወቅ ነው።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0