ኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ሕብረታቸውን በገንዘብ ለመደገፍ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣል ጀመሩ
19:12 31.03.2025 (የተሻሻለ: 19:44 31.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ሕብረታቸውን በገንዘብ ለመደገፍ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣል ጀመሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ሕብረታቸውን በገንዘብ ለመደገፍ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣል ጀመሩ
ይጣላል የተባለው የ0.5 በመቶ ቀረጥ ከሶስቱ የሳህል ሀገራት ጥምረት አባል ሀገራት ውጪ በሆኑ ሁሉም ምርቶች (ሰብዓዊ ያልሆኑ) ላይ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል።
ይህም የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን (ኢኮዋስ) ከሚሸፍነው ሰፊው የምዕራብ አፍሪካ ክልል ጋር የነበረውን ነፃ የንግድ ልውውጥ በይፋ እንዲያበቃ ያደርጋል።
በ2023 በቅድሚያ የፀጥታ ትብብር ሆኖ የተቋቋመው ኤኢኤስ፤ ወደ ሳህል ሀገራት ፌዴሬሽንነት በማደግ የተዋሃደ የባዮሜትሪክ ፓስፖርት እና የጠበቀ ትሥሥር ያለው ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ሕብረት ለመመሥረት እየሠራ ይገኛል።
@sputnik_ethiopia