ኒጀር ከቻድ ሀይቅ የጋራ ወታደራዊ ኃይል መውጣቷን አስታወቀች
17:51 31.03.2025 (የተሻሻለ: 18:14 31.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር ከቻድ ሀይቅ የጋራ ወታደራዊ ኃይል መውጣቷን አስታወቀች
የኒጀር መንግሥት በቻድ ሀይቅ አካባቢ እስላማዊ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ከተቋቋመው የጋራ ጦር ኃይል ለመውጣት የወሰነው የሀገሪቱን የነዳጅ ሀብት ለመጠበቅ እንደሆነ ገልጿል።
ውሳኔው በሲቪሊያን እና በኃይል ተቋማት እንዲሁም በአጋዴም-ቤኒን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጥቃቶች መፈፀማቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ በተጨማሪም በአዲሱ የኒጀር ወታደራዊ መንግሥት የአምስት ዓመት የሽግግር እቅድ መሠረት ውስጣዊ ደህንነት ትኩረት እንደተሰጠው ተጠቁሟል።
ናይጄሪያ ፣ ቻድ ፣ ካሜሩን ፣ ቤኒን
እና ኒጀርን የሚያካትተው የጋራ ጦር ኃይል እ.አ.አ ከ2015 ጀምሮ በቅንጅት ችግር ምክንያት ቦኮ ሃራም* እና ዳኢሽን* በአግባቡ ለመዋጋት አልቻለም።
የኒጀር መውጣት የጋራ ኃይሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ግልጽ አይደለም፡፡ የጋራ ጦር ኃይሉ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም። በተመሳሳይ ቻድ ባለፈው ዓመት በአንድ ጦር ሠፈር ላይ ከደረሰ ከባድ ጥቃት በኋላ ከጋራ ኃይሉ እንደምትወጣ አስተንቀቃ ነበር።
*ሩሲያን ጨምሮ በብዙ ሀገራት ውስጥ የተከለከሉ የሽብር ድርጅቶች
@sputnik_ethiopia