የቻይና እና ሩሲያ ግንኙነት ፅኑ እንደሆነና በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ላይ ሚዛን መፍጠሩን እንደሚቀጥል ባለሙያዎች ተናገሩ
16:50 31.03.2025 (የተሻሻለ: 17:14 31.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቻይና እና ሩሲያ ግንኙነት ፅኑ እንደሆነና በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ላይ ሚዛን መፍጠሩን እንደሚቀጥል ባለሙያዎች ተናገሩ
"በቻይና እና ሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ ውስጣዊ አንቀሳቃሽ ኃይል እና ልዩ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው። በየትኛውም ሶስተኛ ሀገር ላይ ያልተነጣጠረና በሶስተኛ ሀገር ተጽዕኖ ሥር የሚወድቅ አይደለም" ሲሉ የምስራቅ ቻይና መደበኛ ዩኒቨርሲቲ የፓርቲ ኮሚቴ ፀሐፊ ሜይ ቢንግ ተናግረዋል።
ሜይ በቫልዳይ የውይይት ክለብ የሩሲያና ቻይና ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት የቻይናም ሆነ የሩሲያ የውስጥ ፖሊሲዎች እና የልማት ግቦች የረጅም ጊዜ ባህሪ ያላቸው ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ ቻይና መደበኛ ዩኒቨርሲቲ የሩሲያ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ፌንግ ሻኦሌይ አብዛኛዎቹ ቻይናውያን ሩሲያን ታማኝ አጋር አድርገው እንደሚመለከቱ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፉት 30 እና 40 ዓመታት ውስጥ በተከሰቱ ዓለም አቀፍ ለውጦች እና ተከታታይ ግጭቶች የተቀረፀ ነው ሲሉም አክለዋል።
@sputnik_ethiopia