ቴህራን ከዋሽንግተን ጋር በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙርያ በቀጥታ ለመደራደር ፈቃደኛ አይደለሁም አለች
15:04 31.03.2025 (የተሻሻለ: 15:24 31.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቴህራን ከዋሽንግተን ጋር በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙርያ በቀጥታ ለመደራደር ፈቃደኛ አይደለሁም አለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቴህራን ከዋሽንግተን ጋር በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙርያ በቀጥታ ለመደራደር ፈቃደኛ አይደለሁም አለች
የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዚሽኪያን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጻፉት ደብዳቤ ቴህራን በሶስተኛ ወገን ሽምግልና ብቻ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
"ኢራን ከንግግር በጭራሽ ርቅ አታውቅም፤ በዚህ ረገድ ዋሽንግተን የገባችውን ግዴታ መጣሷ አደናቃፊ ነበር፡፡ ይህም በእርግጥ መካስ አለበት፤ በአሜሪካ ላይ ያለው እምነትም መመለስ አለበት። እንዲህ ያሉ የአሜሪካ ድርጊቶች የወደፊት ድርድሮችን አካሄድ ይወስናሉ" ማለታቸውን ኢርና የዜና ወኪል ዘግቧል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቺ ቴህራን ለትራምፕ ደብዳቤ በኦማን በኩል በይፋ ምላሽ መስጠቷን ሐሙስ ዕለት አስታውቀዋል።
@sputnik_ethiopia