በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ የካርቱምን ነፃ መውጣት አከበረ
14:04 31.03.2025 (የተሻሻለ: 14:24 31.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ የካርቱምን ነፃ መውጣት አከበረ
'የሉዓላዊነት ምልክት' የሆነችውን ካርቱም መልሶ መቆጣጠር ለሀገሪቱ በጣም ወሳኝ ነው ሲሉ በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሐመድ አል-ጋዛሊ ኤልቲጋኒ ሲራጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የካርቱም ነፃ መውጣት ለሰላም አዲስ ምዕራፍ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ ሠራዊቱ እና ሕዝቡ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ቁርጠኛ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቅቡል እቅድ እንደሌለው እና ዜጎች ከእነርሱ ጋር ደህንነት እንደማይሰማቸው በመጥቀስ፤ በሱዳን መፃኢ ዘመን ቦታ ስለማይኖራቸው ብቸኛ አማራጫቸው እጅ መስጠት ነው ብለዋል።
"ይህ ከኮርዶፋን እና ዳርፉር በመጀመር፤ ሁሉንም የሱዳን ክልሎች ነፃ ለማውጣት እና እኩል የሀብት እና የስልጣን ክፍፍል ያለበት አዲስ የሰላም ዘመን ለመመስረት የሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ይመስለኛል" ሲሉ በባውማን ሞስኮ ስቴት የቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት አቦበክር መሐመድ አቦበክር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ይህ ድል ምንም እንኳን ምልክታዊ ቢሆንም የሱዳን ጦር አድካሚውን ጦርነት እንዳሸነፈ ያሳያል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ "ትዕግስት፣ ቁርጠኝነት እና ጠንክሮ መሥራት በመጨረሻ ፍሬ አፍርቷል" ብለዋል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ