19ኛዋ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ19ኛዋ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች
19ኛዋ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2025
ሰብስክራይብ

19ኛዋ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች

ኤምቪ አባይ ሁለት የተባለችው የኢትዮጵያ መርከብ ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 55 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ በጅቡቲ ወደብ ማራገፍ መጀመሯን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታውቋል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከተቃደው 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እሰከ መጋቢት 21 ድረስ 11 ሚልየን ኩንታል የሚጠጋ የአፈር ማዳበሪያ በ19 መርከቦች ተጭኖ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ900 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደተጓጓዘ እና 118 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ደግሞ በጅቡቲ ወደብ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በ19 መርከቦች ከተጫነው ውስጥ 682 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ዳፕ እንዲሁም ከ336 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ እንደሆነ ከመሥሪያ ቤቱ የተገኘው መርጃ ያሳያል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0