ለህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከዳያስፖራው 3 ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ
20:27 30.03.2025 (የተሻሻለ: 20:44 30.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከዳያስፖራው 3 ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከዳያስፖራው 3 ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ዳያስፖራው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ግዢና በተለያየ መንገድ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለግድቡ ግንባታ ማጠናቀቂያ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ከዳያስፖራው 3 ሚሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቀዋል።
ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባሉት አርባ አምስት ቀናት ግማሽ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መሰብሰቡንም ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia