ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በመተካት ባለፉት ስምንት ወራት 2.
19:43 30.03.2025 (የተሻሻለ: 20:14 30.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በመተካት ባለፉት ስምንት ወራት 2.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማዳኗ ተናገረ
ሀገሪቱ 96 ቁልፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት መለየቷን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡልልታ ተናግረዋል።
መንግሥት በውጭ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ማቃለል፣ በቂ የሥራ እድል መፍጠር እና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሳደግ ላይ በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ባለፈው የበጀት ዓመት 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምረቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉንም አስታውቀዋል። በሀገር ውስጥ የሚመረቱ እቃዎች የገበያ ድርሻ እያደገ መጥቶ ከ43 በመቶ በላይ መድረሱን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia