ሃንጋሪ ከሩሲያ ኃይል በምታስተላልፍበት መሠረተ ልማት ላይ የሚደረግ ጥቃት በሉዓላዊነቴ ላይ እንደተቃጣ አድርጌ እቆጥረዋለሁ አለች
18:14 30.03.2025 (የተሻሻለ: 18:44 30.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሃንጋሪ ከሩሲያ ኃይል በምታስተላልፍበት መሠረተ ልማት ላይ የሚደረግ ጥቃት በሉዓላዊነቴ ላይ እንደተቃጣ አድርጌ እቆጥረዋለሁ አለች
"ዩክሬን በድሩዝባ የነዳጅ መስመር እና ተያያዥ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረሷ ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል አንዳንዴም ለሙሉ ቀናት አጋጥሞናል" ሲሉ የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲያርቶ ለአርአይኤ ኖቮስቲ ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን በኃይል ማመንጫ ተቋማት ላይ ጥቃት ከመፈጸም ለመታቀብ በደረሱት ስምምነት ደስተኛ እንደሆኑ የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ዝርዝር ሩሲያ ለሃንጋሪ ነዳጅ እና ጋዝ የምታቀርብበት ማስተላለፊያ መስመርን እንደሚያካትት ጠቁመዋል።
"የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሩሲያ አየር ኃይል ወይም የአየር መከላከያ ከዩክሬን የተነሳ ሰው አልባ አውሮፕላን በተርኪሽ የነዳጅ መስመር ላይ የተደረገ ጥቃትን መከላከላቸውን ገልፀውልናል" ሲሉ ሲያርቶ ተናግረዋል።
@sputnik_ethiopia