የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ወታደሮች አማፂያን ከያዙት የኮንጎ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጎማ ከተማ ወታደሮቹን ለማስወጣት ተሰማማ
14:54 30.03.2025 (የተሻሻለ: 15:14 30.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ወታደሮች አማፂያን ከያዙት የኮንጎ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጎማ ከተማ ወታደሮቹን ለማስወጣት ተሰማማ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ወታደሮች አማፂያን ከያዙት የኮንጎ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጎማ ከተማ ወታደሮቹን ለማስወጣት ተሰማማ
በደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) ወታደሮች እና በኤም23 አማፂያን መካከል በጎማ ከተማ ከተደረገ ስብሰባ በኋላ የወጣ መግለጫ እንደሚያመለክተው ሁለቱ አካላት ግጭቶችን ለማቆም እና የሳዳክ ወታደራዊ ኃይሎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከከተማው እንዲወጡ ተስማምተዋል።
ስምምነቱ በአሁኑ ጊዜ በጎማ አውሮፕላን ማረፊያ የሰፈሩት የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች መሳሪያቸውን ይዘው ከማረፊያው እንደሚወጡ ይገልጻል። በተመሳሳይ ደቡብ አፍሪካ በጥር ወር በተካሄደው ግጭት ጉዳት የደረሰበትን የጎማ አውሮፕላን ማረፊያ ለመጠገን ቃል ገብታለች።
የሳድክ ወታደሮች የሚወጡበት ቀን እስካሁን አልተወሰነም። የሳዳክ እና የኤም23 ተወካዮች በቅርቡ በጎማ እንደገና እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል።
@sputnik_ethiopia