ሩሲያ በምያንማር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት የማንዳሌ ክልል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን ላከች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በምያንማር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት የማንዳሌ ክልል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን ላከች
ሩሲያ በምያንማር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት የማንዳሌ ክልል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን ላከች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.03.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በምያንማር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት የማንዳሌ ክልል የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን ላከች

የተላከው ቡድን 20 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን፣ የአነፍናፊ ውሻ አስልጣኞችን እና የሰው አልባ ስርዓት ኦፕሬተሮችን ያካተተ ሲሆን ተጨማሪ 10 የሩሲያ የአደጋ ግዜ ሠራተኞች በመሠረተ ልማቶች እና መንገዶች ላይ የደረሠውን ጉዳት ለመገምገም አደጋ ወደተከሰተባቸው ስፍራዎች መጓዛቸውን የሩሲያ የአደጋ ጊዜ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል።

የሩሲያ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ቡድን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መሠረት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የአደጋ ግዜ ምላሽ ማዕከል አካል እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በምያንማር አርብ ዕለት የተከሰተው በሬክተር ስኬል 7.7 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥቅ ባንግላዴሽ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ታይላንድ ድረስ ንዝረቱ ተሰምቷል። በቅርብ ጊዜ መረጃ መሠረት መሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው የሟቾች ቁጥር 1 ሺህ 644 የደረሰ ሲሆን 3 ሺህ 408 ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 139 ሰዎች ጠፍተዋል። ሩሲያ እና ቤላሩስን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የነፍስ አድን ሥራውን እያገዙ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0