የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትን ጠየቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትን ጠየቁ
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትን ጠየቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.03.2025
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትን ጠየቁ

ቲኑቡ ከ73ኛ ዓመት ልደታቸው በፊት ለሀገሪቱ ደህንነት ለመጸለይ በተዘጋጀው ልዩ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከሌሎች የእምነቱ ተከታዮች ጋር ተሳትፈዋል። የሀገሪቱ መሪ ሆነው ለማገልገል በመታደላቸው ምሥጋናቸውን በመግለፅ ለናይጄሪያ መረጋጋት፣ ሰላም እና ለሁሉም ዜጎቿ ደህንነት እንደጸለዩ ተናግረዋል።

አክለውም የጸሎት ሥነ-ሥርዓቱ ናይጄሪያን ለማገልገል ያላቸውን መነሳሳት እና ቁርጠኝነት ያደሰ መሆኑን ገልጸው፤ እድገትን ለማስመዝገብ ጠንክሮ መሥራት እና ጸሎት ወሳኝ ነገሮች ናቸው ብለዋል። እስካሁን ለተመዘገበው ለውጥ ለፈጣሪ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንቱ በልዩ አማካሪያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ናይጄሪያውያን ባሉበት ቦታ ወይም በሚያመልኩበት ቦታ ሳይወሰኑ፤ ለሀገሪቱ አንድነት እና የጋራ ዕጣ ፈንታ በመንፈስ የጸሎት ሥነ-ሥርዓቱን እንዲቀላቀሉ አበረታትተዋል። መንግሥታቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለማራመድ፣ ብሔራዊ ደህንነትን ለማጠናከር እና ለሁሉም ዜጎች እድሎችን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት የናይጄሪያ ሕዝብ ለሚያደርገው ጠንካራ ድጋፍም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0