ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የባሕረኞች ማሠልጠኛ አካዳሚ ልትከፍት ነው
17:12 29.03.2025 (የተሻሻለ: 17:44 29.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የባሕረኞች ማሠልጠኛ አካዳሚ ልትከፍት ነው
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የማሰልጠኛ አካዳሚውን ለመክፈት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር ተፈራርሟል።
አካዳሚው ከባቦጋያ ሎጅስቲክሰ እና ማሪታይም አካዳሚ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ማሪታይም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀጥሎ ለሀገሪቱ ሶስተኛው ማሰልጠኛ እንደሚሆን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ኢትዮጵያ በ2022 በሎጅስቲክስ አፈፃፀም ከአፍሪካ ቀዳሚ እንድትሆን ለማድረግ እንዲሁም ባሕረኞችን አሠልጥኖ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከመጀመሪያዎቹ አምስት የዓለም ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እየሠራ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል።
@sputnik_ethiopia