የአፍሪካ ሀገራት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በድጋሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ሲሉ አልጄሪያዊው ባለሙያ ተናገሩ
14:02 29.03.2025 (የተሻሻለ: 14:34 29.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ሀገራት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በድጋሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ሲሉ አልጄሪያዊው ባለሙያ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በድጋሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ሲሉ አልጄሪያዊው ባለሙያ ተናገሩ
"የአፍሪካ አህጉር እርምጃውን በጉጉት እየጠበቀ ነው፤ በተለይም የምግብ እጥረት የገጠማቸው ደቡባዊ የአህጉሪቱ ሀገራት። ይህ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የእህል ፍላጎቶችን ለመሸፈን ጥሩ አጋጣሚ ነው" ሲሉ በአልጄሪያ ፈርሃት አባስ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፋሬስ ሃባቼ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በሩሲያ የእህል ምርት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት ሩሲያ የአፍሪካ ቀዳሚ ምግብ አቅራቢ መሆኗን እንደሚያጠናክር ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ እ.አ.አ 2024 ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የለገሰችውን 200 ሺህ ቶን እህል አስታውሰዋል።
የፑቲን እና ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ሩሲያ እና አሜሪካ የጥቁር ባህር ስምምነትን በድጋሚ ለመጀመር ተስማምተዋል። ስምምነቱ በሩሲያ የግብርና ባንክ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ጨምሮ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው።
@sputnik_ethiopia