የሩሲያ የገንዘብ ማስተላለፊያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የፊንቴክ ዘርፍ ለመሠማራት ፍላጎቱን ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የገንዘብ ማስተላለፊያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የፊንቴክ ዘርፍ ለመሠማራት ፍላጎቱን ገለፀ
የሩሲያ የገንዘብ ማስተላለፊያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የፊንቴክ ዘርፍ ለመሠማራት ፍላጎቱን ገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.03.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የገንዘብ ማስተላለፊያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የፊንቴክ ዘርፍ ለመሠማራት ፍላጎቱን ገለፀ

የሩሲያ ዩኒቴለር ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጉዶቭ ሮማን በሞስኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ጋር በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጉዶቭ ሮማን ኩባንያቸው በፊንቴክ እና ቱሪዝም ዘርፍ ያሉ እድሎችን የመዳሰስ ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።

አምባሳደር ገነት በኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት ግቦች በተለይም በዲጂታል ኢኮኖሚው ዙሪያ ገለፃ ማድረጋቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ እድሎች እንዳሉት ጠቁመዋል።

አምባሳደር ገነት ኩባንያው ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከመንግሥት እና ከግሉ ዘርፍ ጋር ለመተባበር ያሚያስችሉ አማራጮችን እንዲመለከት ጋብዘዋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0