ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፖለቲካዊ ጥቅም ነው የሚመራው ሲሉ የቀድሞ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ
17:30 28.03.2025 (የተሻሻለ: 18:04 28.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፖለቲካዊ ጥቅም ነው የሚመራው ሲሉ የቀድሞ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ
የቀድሞ የአውሮፓ ፓርላማ አባል እና የሕግ ባለሙያ ጂልበርት ኮላርድ "አይሲሲ ስልጣኑን እንዳጣ እና አንድ ቀን መጥፋቱ እንደማይቀር" ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"አይሲሲ በፖለቲካዊ ጥቅም መዳፍ ውስጥ ነው፤ በዚህም ለተቋሙ ምንም ዓይነት የፍትሃዊነት ቁመና ልንሰጠው አንችልም" ብለዋል።
አይሲሲ “የተለዩ ኢላማዎች” እንዳሉትና ጉዳዮቹንም አድሎአዊ በሆነ መልኩ እንደሚያቅረብ የተናገሩት ጂልበርት ኮላርድ፤ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ “በጣም አወዛጋቢ ግለሰብ ናቸው” ሲሉም አስረግጠዋል።
"ስለዚህ በእኔ እምነት ተቋሙ ወይ መቅረት አለበት አልያም ሙሉ በሙሉ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል" ብለዋል።
@sputnik_ethiopia