አፍሪካ ሕብረት በሶማሊያ በሚያሠማራው አዲስ ተልዕኮ የኃይል አደረጃጀት እና የስምሪት እቅድ ዙሪያ ስብሰባ አካሄደ
11:33 28.03.2025 (የተሻሻለ: 11:54 28.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ ሕብረት በሶማሊያ በሚያሠማራው አዲስ ተልዕኮ የኃይል አደረጃጀት እና የስምሪት እቅድ ዙሪያ ስብሰባ አካሄደ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ ሕብረት በሶማሊያ በሚያሠማራው አዲስ ተልዕኮ የኃይል አደረጃጀት እና የስምሪት እቅድ ዙሪያ ስብሰባ አካሄደ
“ከዚህ ስብሰባ ቁልፍ ውጤቶች አንዱ ለሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውጤታማነት የሚያስፈልጉ የወታደር እና ፖሊስ ኃይሎች ዝርዝርን በተመለከት የአስፈላጊ ጦር ክፍል መግለጫን ማጠናቀቅ ነው” ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ልዑካን ቡድን መሪ ብሬጋዴር ጄኔራል ቢሊ አትዎኪ ዊንተር ተናግረዋል፡፡
ተልዕኮው አልሸባብን* ውጤታማ በሆነ መንገደ ለመመከት የሚያስችሉ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኃይሎችን፣ ታክቲካል የጦር ቡድኖችን፣ የመረጃ፣ ክትትልና የስለላ ቡድኖችን፣ የአቪዬሽን አጋዦችን እና የፖሊስ አካላትን እንደሚያካትት የአፍሪካ ሕብረት ገልጿል።
ስብሰባው የዘርፍ ድንበሮችን፣ የዘመቻ ዞኖችን፣ የወታደር እና የፖሊስ ስምሪት የማጠናቀቂያ ሥራዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር መግለጫው አክሎ ገልጿል።
በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ የቀድሞውን የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ የተካ ሲሆን ከሰኔ 24 በኋላ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
*በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገሮች የታገደ አሸባሪ ድርጅት
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ