የአሜሪካ የስለላ ተቋም ሲአይኤ የሙሴ ጽላት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ በምናብ ምልከታ እንዳረጋገጠ የሚያሳይ ሰነድ ይፋ ሆነ
14:55 27.03.2025 (የተሻሻለ: 20:15 27.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ የስለላ ተቋም ሲአይኤ የሙሴ ጽላት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ በምናብ ምልከታ እንዳረጋገጠ የሚያሳይ ሰነድ ይፋ ሆነ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ የስለላ ተቋም ሲአይኤ የሙሴ ጽላት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ በምናብ ምልከታ እንዳረጋገጠ የሚያሳይ ሰነድ ይፋ ሆነ
ሰነዱ የስለላ ተቋሙ እ.አ.አ 1988 ባካሄደው 'የርቀት ምልከታ' ሙከራ የአግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሆነው የሙሴ ጽላት በኢትዮጵያ እንደሚገኝ ማረጋገጡን ይገልፃል።
የሲአይኤ ሰነድ ነገሮችን ከሩቅ ሆነው የማየት ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች የታቦቱን መገኘ እንደለዩ አመላክቷል። የሩቅ ተመልካቾቹ ፅላቱ በእንጨት፣ ወርቅ እና ነሃስ ከተሠራ ሳጥን ወስጥ እንደሚገኝ እና የሚጠብቁት አካላት እንዳሉ ገልፀዋልም ተብሏል።
የሙሴ ጽላት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የአክሱም ከተማ እንደሚገኝ ይታመናል።
@sputnik_ethiopia