የሱዳን ጦር የካርቱም አየር ማረፊያን መልሶ ተቆጣጠረ
15:58 27.03.2025 (የተሻሻለ: 20:15 27.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን ጦር የካርቱም አየር ማረፊያን መልሶ ተቆጣጠረ
የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በአልጀዚራ ብሮድካስተር በተለቀቀ ቪዲዮ “ካርቱም ነፃ ወጥታለች” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የካርቱም አየር ማረፊያ ግጭቱ ከጀመረበት እ.አ.አ ሚያዚያ 2023 ጀምሮ በቅጽል ስማቸው “ሄሚቲ“ ተብለው በሚጠሩት ኮማንደር ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ቁጥጥር ስር ቆይቷል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በአሁኑ ሰዓት ከከተማዋ በድልድይ አቋርጦ እየወጣ ይገኛል ሲል አልጀዚራ አክሎ ዘግቧል።
በጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል። ጦሩ ባለፈው አርብ የፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥቱን በተሳካ ሁኔታ መልሶ መቆጣጠሩ ይታወሳል።
ቪዲዮው ሁለት የሱዳን ወታደሮች በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሱዳንን ባንዲራ ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ያሳያል።
@sputnik_ethiopia