ኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች
ኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.03.2025
ሰብስክራይብ

ኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች

“ፕሬዝዳንት ዊልያም ሳሞኢ ሩቶ እና የኬኒያ ሪፐብሊክ ለሀገራችን ነጻ ሀገርነት እውቅና ለመስጠት ለወሰዱት ታሪካዊ ውሳኔ የኮሶቮ ሪፐብሊክ ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች። ይህ እውቅና በሀገሮቻችን መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር እና ለተሻሻለ የሁለትዮሽ ትብብርም መንገድ የሚከፍት ነው" ሲሉ የኮሶቮ ፕሬዝዳንት ቪዮሳ ኦስማኔ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡

የሰርቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የኬኒያን ውሳኔ አጥብቆ አውግዟል።

ሚኒስቴሩ አክሎም “ይህ እርምጃ በግልፅ የዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ እና ለሰርቢያ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ዋስትና የሚሰጠውን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1244 በቀጥታ የሚተላለፍ ነው" ብሏል።

ሰርቢያ ለኮሶቮ ነጻ ሀገርነት እወቅና የማትሰጥ ሲሆን ግዛቷንም ኮሶቮ እና ሜቶሂጃ ክልል ብላ ትጠራለች። በኮሶቮ ሰሜናዊ ክፍል የሚኖረው ከፍተኛ የሰርብ ማሕበረሰብ አብዛኛውን ግዜ በሰርቢያ እና በኮሶቮ መካከል የሚፈጠረውን የዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ገፈት እንደሚሸከም እና አግላይ ነው የሚለውን የኮሶቮ ፖሊሲ እንደሚቃወም ይነገራል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኬኒያ ራሷን እንደ ነጻ ሀገር ላወጀችው ኮሶቮ እውቅና ሰጠች - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0