ከሶስት አራተኛ በላይ የሚሆኑ ዩክሬናውያን በእንደራሴዎቻቸው ላይ እምነት እንደሌላቸው የሕዝብ አስተያየት መስጫ አመላከተ
18:16 27.03.2025 (የተሻሻለ: 20:14 27.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከሶስት አራተኛ በላይ የሚሆኑ ዩክሬናውያን በእንደራሴዎቻቸው ላይ እምነት እንደሌላቸው የሕዝብ አስተያየት መስጫ አመላከተ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከሶስት አራተኛ በላይ የሚሆኑ ዩክሬናውያን በእንደራሴዎቻቸው ላይ እምነት እንደሌላቸው የሕዝብ አስተያየት መስጫ አመላከተ
የዩክሬን ራዙምኮቭ ማዕከል ያካሄደው የዳሰሳ ጥናት 79.2 በመቶ የሚሆኑ ዩክሬናውያን የመንግሥት ባለስልጣናትን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንደማያምኑ፣ 13.3 በመቶ የሚሆኑት ባለስልጣናቱን እንደሚያምኑ እና 7.5 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች ለጥያቄው መልስ መስጠት እንዳዳገታቸው አሳይቷል።
በሌላ በኩል 70.7 በመቶ ዩክሬናውያን በመንግሥታቸው ላይ እምነት የሌላቸው ሲሆን 22.5 በመቶ የሚሆኑት መንግሥታቸውን ያምናሉ።
ቬርኮቭና ራዳ (የሀገሪቱ ብቸኛ የሕግ አውጪ ምክር ቤት) የ76.7 በመቶ ዩክሬናውያንን እምነት ያጣ ሲሆን 17.8 በመቶ የሚሆኑት ለፓርላማው ያላቸውን እምነት ሲገልፁ 5.5 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች መልስ ለመስጠት እንዳዳገታቸው ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia