ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ሺህ ኪ.

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ሺህ ኪ
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ሺህ ኪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.03.2025
ሰብስክራይብ

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ሺህ ኪ.ግ በላይ ዓሳ በየቀኑ እየተመረተ እንደሆነ ተገለፀ

በግድቡ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው የዓሳ ዝርያዎች እንደሚገኙና በቀን ከ14 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ ዓሳ እየተመረተ እንደሆነ ተገልጿል።

በግብርና ሚኒስቴር የዓሳ ልማት ዴስክ ኃላፊ ፋሲል ዳዊት ዘርፉ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ለሥራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ማለታቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።

በግድቡ በጣም ተፈላጊ የሆነው ናይል ፐርች እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተወዳጅ የሆነው ቀረሶ የዓሳ ዝርያ በስፋት እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓሳ ምርት ዙሪያ 64 ማኅበራት እንደተደራጁ እና 23ቱ ማኅበራት ከውዲሁ የሥራ እድል መፍጠር እንደጀመሩም በዘገባው ተመላክቷል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0