የጉምሩክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት ሚናዋን እንድትወጣ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጉምሩክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት ሚናዋን እንድትወጣ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ
የጉምሩክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት ሚናዋን እንድትወጣ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.03.2025
ሰብስክራይብ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት ሚናዋን እንድትወጣ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ

ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ እና ኬንያ የአንድ አለቅ የድንበር ጣቢያዎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡ ውይይቱ በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደር ጆርጅ አሪና፣ የዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል እንደተደረገ የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከዓመታት በፊት አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከል ተደጋጋሚ ፍተሻዎችን በማስቀረት የተፋጠነ የጉምሩክ አገልግሎት እንዲኖር ማስቻሉን አንስተዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ውህደት ግንባር ቀደም ሚናዋን እንድትወጣ ኮሚሽኑ የበኩሉን ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ተጨማሪ የጋራ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ሱፍቱ እና ራሙ በሚባሉ የድንበር አካባቢዎች ለመገንባት ስለሚቻልበት ሁኔታም መክረዋል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0