የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለጅቡቲ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዳጠናቀቀ ገለጸ
10:56 27.03.2025 (የተሻሻለ: 11:14 27.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለጅቡቲ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዳጠናቀቀ ገለጸ
በሁለተኛ ምዕራፍ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት 46 ኪ.ሜ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 28 ትራንስፎርመሮች የማስቀመጥ ሥራ እንደተከናወነ አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ 8 ሜጋዋት ኃይል፣ 36 ኪ.ሜ የመስመር ዝርጋታ እንዲሁም 8 ባለ 1250 ኬቪኤ ትራንስፎርመር ተከላ መከናወኑን ተቋሙ ገልጿል፡፡
በሁለቱም ምዕራፍ በተከናወነው የመስመር ዝርጋታ በአጠቃላይ 82 ኪ.ሜ መስመር እንደተዘረጋ እና 36 ትራንስፎርመሮች እንደተቀመጡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ ሥራ ተጠናቆ ርክክብ እየተደረገ እንደሆነ አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል።
@sputnik_ethiopia