የኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ቀንሷል አለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ቀንሷል አለ
የኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ቀንሷል አለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.03.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ቀንሷል አለ

ሁለተኛ ስብሰባውን በትናንትናው እለት ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ፤ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት መቀነሱንና በየካቲት ወር መጨረሻ 15.0 በመቶ መድረሱን አስታውቋል።

ኮሚቴው ምግብ-ነክ የዋጋ ግሽበት በየካቲት ወር 2017 መጨረሻ 14.6 በመቶ እንደደረሰ የገለፀ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 31 በመቶ ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ያነሰ ነው ብሏል።

ምግብ-ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ቀንሶ 15.6 በመቶ መድረሱንም ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ፣ የግብርና ምርት መሻሻልና በአስተዳደራዊ ዋጋዎች ላይ እየተወሰደ ያለው ማሻሻያ ቀስ በቀስ መተግበሩ ለዋጋ ግሽበቱ መቀንስ ምክንያት ናቸው ተብሏል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0