አሜሪካ 70 በሚሆኑ የደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኢራን ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች
20:00 26.03.2025 (የተሻሻለ: 20:44 26.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ 70 በሚሆኑ የደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኢራን ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ 70 በሚሆኑ የደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኢራን ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች
በመጪው አርብ የሚታተመው የኢንዱስትሪ እና ደህንነት ቢሮ ውሳኔ የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ቢሮ ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ወይም የውጭ ፖሊሲ ጥቅም በተቃራኒው ተንቀሳቅሰዋል ባላቸው ኩባንያዎች ላይ የወጪ ንግድ ገደብ እንደሚጥል ያመለክታል።
አሴንሶ አቪዬሽን፣ ብሉ ስካይ አቪዬሽን እና ዊንግማን ኮንሴፕት የተባሉ ሶስት የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች የእገዳው ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት "ከደቡብ አፍሪካ የሙከራ በረራ አካዳሚ ጋር ባላቸው ግንኙነት እና የምዕራባውያን እና ኔቶን መረጃ በመጠቀም የቻይና ጦር ኃይሎችን ስልጠና በመስጠታቸው" ነው ያለው ቢሮው፤ የበረራ አካዳሚው እ.አ.አ 2023 ሰኔ ወር ጀምሮ በእገዳ ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ጨምሮ ገልጿል።
@sputnik_ethiopia