የአፍሪካ ሕብረት ሩሲያ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት እየተጫወተችው ያለውን ሚና አወደሰ
20:16 26.03.2025 (የተሻሻለ: 20:44 26.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ሩሲያ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት እየተጫወተችው ያለውን ሚና አወደሰ
በኢትዮጵያም የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ከአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በዛሬው እለት ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ውይይቱ በተለይም በሱዳን እና ሶማሊያ ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አስታውቋል።
አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ሩሲያ በአፍሪካ ውህደት ዙሪያ አስተዋጽኦ እና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነችም ገልፀዋል። አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እነዚህን የሩሲያ ጥረቶች እንዳደነቁ ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።
@sputnik_ethiopia