ሁቲዎች በቀይ ባሕር የአሜሪካ የጦር መርከቦች እና በእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሁቲዎች በቀይ ባሕር የአሜሪካ የጦር መርከቦች እና በእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታወቁ
ሁቲዎች በቀይ ባሕር የአሜሪካ የጦር መርከቦች እና በእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.03.2025
ሰብስክራይብ

ሁቲዎች በቀይ ባሕር የአሜሪካ የጦር መርከቦች እና በእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታወቁ

"የሚሳይል ኃይሎች፣ የሰው አልባ ስርዓት ኃይሎች እና የባህር ኃይሎች ባካሄዱት የጋራ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በትሩማን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ በሚመሩ የጠላት ጦር መርከቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል...የሰው አልባ ስርዓት ኃይሎች በኃይል በተያዝው ጃፋ አካባቢ የሚገኙ የጠላት እስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ጥቃቱም አላማውን አሳክቷል" ሲሉ የሁቲ ጦር ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ ተናግረዋል።

በጦር መርከቦቹ ላይ የተካሄደው ጥቃት በርካታ ሰዓታት እንደፈጀም ጠቁመዋል።

የሁቲዎች መሪ አብዱል ማሊክ አል-ሁቲ አሜሪካ በየመን ላይ ጥቃት ማድረሷን ከቀጠለች ሁሉም የአሜሪካ እና የእስራኤል መርከቦች የቀይ ባሕር እና የአረብ ባሕርን ማቋርጥ አይችሉም ሲሉ በዚህ ወር መጀመሪያ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0