የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ሰጥቶ በመቀበል መርህ ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ
18:20 26.03.2025 (የተሻሻለ: 18:44 26.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ሰጥቶ በመቀበል መርህ ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ አንገብጋቢ እንደሆነ እና ሀገሪቱ ዘላቂ እና የተረጋገጠ የባሕር አማራጭ እንደምትሻ ቃል አቀባዩ ነብያት ጌታቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ይህ የባሕር በር ጥያቄ በሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ተግባራት እየተንጸባረቀ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡
“ሀገሪቱ ዘላቂ እና የተረጋገጠ የባሕር ወደብ ስለሚያስፈልጋት የባሕር በር ጥያቄ ወይም የባሕር መተንፈሻ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ጉዳይ በዲፕሎማሲ እንቀስቃሴዎቻችን ላይ እየተንጸባረቀ ነው” ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዘላቂ የባሕር በር ለማግኘት ጥረቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ነው ቃል አቀባዩ ያስታወቁት፡፡
“ኢትዮጵያ የተረጋገጠ እና ዘላቂ የባሕር በር ማግኘት የምትፈልገው በሰጥቶ መቀበል መርህ መሠረት በሰላማዊ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ነው፡፡ ሀገሪቱ ዘላቂ የባሕር በር የማግኘት ግቧን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት” ሲሉም አክለዋል፡፡
@sputnik_ethiopia