ቦይንግ በማክስ 737 አውሮፕላኖች አደጋ ዙሪያ በተከፈበት የወንጀል ክስ የደረሰውን የጥፋተኝነት ስምምነት ለማቋረጥ ይፈልጋል ተባለ

ሰብስክራይብ

ቦይንግ በማክስ 737 አውሮፕላኖች አደጋ ዙሪያ በተከፈበት የወንጀል ክስ የደረሰውን የጥፋተኝነት ስምምነት ለማቋረጥ ይፈልጋል ተባለ

የወንጀል ክሱ ኩባንያው ከሁለቱ አደጋዎች በፊት ተቆጣጣሪዎችን በማሳሳት ጥፋተኛ ነው የሚል እንደነበር የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ዳኛ በስምምነቱ ውስጥ የተካተተውን የብዝሃነት እና አካታችነት አንቀጽ በማንሳት ስምምነቱን በታህሳስ ወር ውድቅ አድርገውታል። ቦይንግ እና የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ መሥርያ ቤት አዲስ ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር ሲያደርጉ እንደቆዩ ነው የተገለጸው፡፡

በሀምሌ ወር ቦይንግ በተከፈተበት የማጭበርበር ሴራ ወንጀል ክስ ጥፋተኝነቱን አምኖ እስከ 487.2 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ቅጣት ለመክፈል እና የደህንነት እና ሕግ የመከተል ልምዱን ለማሻሻል 455 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለማድርግ ተስማምቶ ነበር፡፡

እ.አ.አ 2018 እና 2019 መነሻቸውን ጃካርታ ኢንዶኔዥያ እና አዲስ አበባ ያደረጉ ተመሳሳይ ሥሪት ያላቸው ማክስ 737 አውሮፕላኖች ተከስክሰው 346 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

የጥፋተኝነት ስምምነቱ ቦይንግ ችግር ባለባቸው የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሮች ዙሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል አቪዬሽን ባልስልጣንን ለማሳሳት በማሴር ወንጀለኛ ያስብለው ነበር፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0