ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር በቀጣናው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትን በኃይል እያስተሳሰረች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ
15:21 26.03.2025 (የተሻሻለ: 15:44 26.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር በቀጣናው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትን በኃይል እያስተሳሰረች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር በቀጣናው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትን በኃይል እያስተሳሰረች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ
ሀገሪቱ ለጅቡቲ፣ ለኬኒያና ለሱዳን ኃይል እያቀረበች እንደሆነና በቅርቡም ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ እንደምትጀምር የተቋሙ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሞገስ መኮንን ጠቁመዋል።
ለጎረቤት ሀገራት እየቀረበ ያለው ኃይል ከሚመነጨው 10 በመቶ በታች ቢሆንም የተቋሙን ከ30 በመቶ በላይ ገቢ እየሸፈነና ለቀጣናዊ ትስስር አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑንም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አህጉሩን በመሠረተ ልማት የማስተሳሰር ዕቅድ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ድርሻውን ለመውጣት እየሠራ እንደሆነ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ሀገራዊ ኃይል የማመንጨት አቅምን ከእጥፍ በላይ ለማሳደግ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ አምስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሆነም አስታውሰዋል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር በቀጣናው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትን በኃይል እያስተሳሰረች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/