ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የባለሙያዎች ቋሚ የምክክር መድረክ በመፍጠር የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስርዓትን ለመቀየር እንደሚሠሩ ገለፁ
14:13 26.03.2025 (የተሻሻለ: 14:44 26.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የባለሙያዎች ቋሚ የምክክር መድረክ በመፍጠር የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስርዓትን ለመቀየር እንደሚሠሩ ገለፁ
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ገነት ተሾመ እና የኢኒስቲትዩቱ ዳይሬክተር እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካይል ፍራድኮቭ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ እንዲሁም በሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እንዳደረጉ በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
በውይይቱ በሀገራቱ የምርምር ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉን ኤምባሲው ጨምሮ ገልጿል።
@sputnik_ethiopia