ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አቀባበል ተደረገላት
13:28 26.03.2025 (የተሻሻለ: 13:44 26.03.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አቀባበል ተደረገላት
ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አዲስ አባል ሀገራት በታንዛንያ አሩሻ ከተማ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ አዲሶቹ አባላት ኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ ምክር ቤቱን በይፋ ተቀላቅለዋል።
ካሜሮን እና ናይጄሪያ በድጋሚ የተመረጡ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው።
ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር አንስቶ በምክር ቤቱ በይፋ በአባልነት ማገልገል እንደምትጀምር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@sputnik_ethiopia