የኤም23 ታጣቂዎች ለቀናል ካሉት የዋሊካሌ ከተማ አሁንም እንደሚገኙ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኤም23 ታጣቂዎች ለቀናል ካሉት የዋሊካሌ ከተማ አሁንም እንደሚገኙ ተነገረ
የኤም23 ታጣቂዎች ለቀናል ካሉት የዋሊካሌ ከተማ አሁንም እንደሚገኙ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.03.2025
ሰብስክራይብ

የኤም23 ታጣቂዎች ለቀናል ካሉት የዋሊካሌ ከተማ አሁንም እንደሚገኙ  ተነገረ

🪖 የኮንጎ ሬዲዮ ጣቢያ ኦካፒ ያጣቀሳቸው የሲቪል ማህበረሰብ ምንጭ እንደገለጹት፤ የኤም23 ቡድን ተጨማሪ ጦር፤ ወታደሮች እና አቅርቦቶችን ጨምሮ፤ ሰኞ ዕለት በሁለት በረራዎች ዋሊካሌ ከተማ በሚገኘው ኪጎማ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከማሲሲ ወረዳ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙት እና ከዋሊካሌ ከተማ ጋር በሚዋሰኑት ሻቡንዳ እና ሙታካቶ መንደሮች በኤም23 አማፂያን እና የመንግሥት ደጋፊ ዋዛሌንዶ ሚሊሻዎች መካከል ሰኞ እለት ከባድ ግጭት እንደተነሳ ተነግሯል።

በምስራቅ ኮንጎ እየተባባሰ በመጣው ቀውስ ምክንያት ከጥር ወር ጀምሮ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች፤ አብዛኞቹ ሴቶች፣ ህጻናት እና አዛውንቶች፤ ወደ ቡሩንዲ እንደተሰደዱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0