ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ አዲስ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ
11:14 26.03.2025 (የተሻሻለ: 11:44 26.03.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ አዲስ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ አዲስ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትሥሥር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በፕሪቶሪያ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሠረት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተቀመጠው የሁለት ዓመት ግዜ ማለቁን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሁለት ዓመት ውስጥ ሥራውን አጠናቆ ስልጣኑን በህዝብ ለተመረጠ መንግሥት ማስረከብ ባለመቻሉ ለተጨማሪ አንድ ዓመት መራዘሙ ግድ ሆኗል ብለዋል።
በዚሁ መሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መሾም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ቢሆንም፤ ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ እንዲሁም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ይችላሉ ብላችሁ የምታምኑትን እጩ ጠቁሙ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
@sputnik_ethiopia