የእስራኤል ጦር በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ ተናገረ

 / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእስራኤል ጦር በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ ተናገረ
የእስራኤል ጦር በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ ተናገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.03.2025
ሰብስክራይብ

የእስራኤል ጦር በሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ ተናገረ

“የእስራኤል መከላከያ ኃይል ከጥቂት ሰዓታት በፊት በወሰደው ጥቃት በታድሙር እና በቲ4 የሶሪያ የጦር ሠፈሮች ላይ የቀሩ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ኢላማ አድርጓል” ሲል የመከላከያ ሠራዊቱ በቴሌግራም ገፁ ይፋ አድርጓል።

የእስራኤል ጦር በታኅሣሥ ወር መጀመሪያ በደማስቆ የመንግሥት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ በቀድሞው የሶሪያ ጦር ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ማደረስ እንደጀመረ የሚታወስ ነው። በበርካታ የሶሪያ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ወታደራዊ የአየር ማረፊያዎች፣ የጦር መሣሪያ መጋዘኖች እና የአየር መከላከያ ሥርዓቶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሟል።

እስራኤል በፓልሚራ ወታደራዊ አየር ማረፊያ እንዲሁም በፓልሚራ እና በሆምስ መካከል በሚገኘው ቲ4 የሶሪያ አየር ኃይል ሠፈር ላይ ከዚህ ቀደም የአየር ድብደባ መፈፀሟ ይታወቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0